በGoogle One በሚቀርበው VPN በመጠቀም የመስመር ላይ ደህንነትዎን ይጨምሩ
በመላ የAndroid፣ iOS፣ Windows እና Mac መሣሪያዎች ላይ ለተጨማሪ የጥበቃ እና ግላዊነት ንብርብር የመስመር ላይ እንቅስቃሴዎን ማመስጠር ይችላሉ።VPN በተመረጡ አገሮች ውስጥ ይገኛል።
ተጨማሪ የመስመር ላይ ጥበቃ
በVPN በGoogle One፣ የመስመር ላይ እንቅስቃሴዎን ለመመስጠር የGoogleን ዓለም አቀፍ ደህንነት ማሳደግ ይችላሉ — የሚጠቀሙበት መተግበሪያ ወይም አሳሽ ምንም ይሁን ምን።
- የአይፒ አድራሻዎን በመደበቅ የመስመር ላይ ክትትልን ይቀንሱ
- ደህንነታቸው ባልተጠበቀ አውታረ መረቦች (እንደ ይፋዊ Wi-Fi ያሉ) ላይ ከሰርጎ-ገቦች መሰለል ይከላከሉ
- ደህንነቱ እና የግል በሆነ ግንኙነት ድሩን ያስሱ1

ሊያምኑት የሚችሉ ደህንነት
ግላዊነት እና ደህንነት ለምንሰራው ነገር ሁሉ ቁልፍ ናቸው።
- Google የአሰሳ እንቅስቃሴዎን ለመከታተል፣ በምዝግብ ማስታወሻ ለመያዝ ወይም ለመሸጥ የቪፒኤኑን ግንኙነት በጭራሽ አይጠቀምም2
- የእኛ ስርዓቶች ማንም ሰው VPNን ተጠቅሞ የመስመር ላይ እንቅስቃሴዎን ከማንነትዎ ጋር ማስተሳሰር እንዳይችል ለማረጋገጥ የላቀ አብሮገነብ ደህንነት አላቸው
- እኛ ስላለን ብቻ አይቀበሉ — የእኛ የደንበኛ ቤተ-ፍርግሞች ክፍት ምንጭ ናቸው፣ እና የእኛ ከመጨረሻ እስከ መጨረሻ ስርዓቶች በገለልተኛ አካል ኦዲት የተደረጉ ናቸው።

ፈጣን አፈጻጸም
VPN በGoogle One በዘርፉ ምርጥ በሚባል የGoogle የአውታረ መረብ አርክቴክቸር የሚደገፍ ነው። በማንኛውም ጊዜ በመላ የእርስዎ መተግበሪያዎች እና አገልግሎቶች ላይ ፈጣን የበይነመረብ ግንኙነትን እያስቀጠሉ ቪፒኤኑን ማስሄድ ይችላሉ።
እንከን-አልባ እና ሊጋራ የሚችል
VPN በGoogle Oneን በቀላሉ ያንቁ እና መዳረሻ ለቤተሰብዎ ያጋሩ፣ እነርሱ የተለየ ሥርዓተ ክወና እየተጠቀሙ ቢሆንም እንኳ።
- VPNን በእርስዎ የAndroid፣ iOS፣ Windows እና Mac መሣሪያዎች ላይ ማግበር ይችላሉ
- ዕቅድዎን ሲያጋሩ የVPN ጥበቃ ለ5 ተጨማሪ ሰዎች ሊቀጠል ይችላል

እንዴት ነው ቪፒኤን የሚሰራው
የእርስዎ አሳሽ እና መተግበሪያዎች መስመር ላይ በተደጋጋሚነት ሚስጥራዊነት ያለው መረጃ መለዋወጥ ይችላሉ። አንዳንድ ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች ጊዜያቸው ያለፈባቸው፣ ደካማ ወይም ምንም ምስጠራ የላቸውም።
በትልልፍ ላይ ሳለ ደህንነቱ ያልተጠበቀ ውሂብ በሰርጎ-ገቦች ሊጠለፍ ይችላል፣ ይህም የእርስዎን ግላዊነት እና አጠቃላይ ደህንነት አደጋ ላይ ሊጥለው ይችላል።
አንድ VPN ሲያነቁ የመስመር ላይ ውሂብዎ ጠንካራ ምስጠራ ባለው ዋሻ ውስጥ በማለፍ የተጠበቀ ይሆናል።
VPN በGoogle One ከሌሎች ቪፒኤኖች ምን የተለየ እንደሚያደርገው እና እንዴት እንደሚጠቀሙበት ይመልከቱ።
VPN በGoogle Oneን መጠቀም ይጀምሩ
VPN በGoogle Oneን ለማግኘት የGoogle One አባል ይሁኑ — በተመረጡ አገሮች ውስጥ ከሁሉም ዕቅዶች ጋር ይገኛል።
1በእርስዎ ክልል ውስጥ የማይገኝ ይዘትን ለማየት የአይፒ አካባቢዎን መቀየር አይችሉም።
2የአገልግሎቱን ጥራት ለማረጋገጥ አንዳንድ አነስተኛ ምዝግብ ማስታወሻ መያዝ ይከናወናል፣ ነገር ግን አውታረ መረብዎ በጭራሽ በምዝግብ ማስታወሻ አይያዝም እና የእርስዎ አይፒ ከእንቅስቃሴዎ ጋር አይጎዳኝም።
3የተኳኋኝ ስርዓተ ክወና ስሪቶችን ለማግኘት እዚህ ይመልከቱ።
2የአገልግሎቱን ጥራት ለማረጋገጥ አንዳንድ አነስተኛ ምዝግብ ማስታወሻ መያዝ ይከናወናል፣ ነገር ግን አውታረ መረብዎ በጭራሽ በምዝግብ ማስታወሻ አይያዝም እና የእርስዎ አይፒ ከእንቅስቃሴዎ ጋር አይጎዳኝም።
3የተኳኋኝ ስርዓተ ክወና ስሪቶችን ለማግኘት እዚህ ይመልከቱ።