የGoogle One አገልግሎት ውል

መጨረሻ የተዘመነው፦ ኦክቶበር 1፣ 2018

1. መግቢያ

Google One አድራሻው 1600 Amphitheatre Parkway, Mountain View, California 94043, USA ላይ በሚገኘው በGoogle LLC («Google» ወይም «እኛ») የሚቀርብ አገልግሎት ሲሆን ለGoogle አገልግሎት ውል ተገዢ ነው። Google One በGoogle አገልግሎት ውል መሠረት «አገልግልት» ሲሆን የሚከተሉት የGoogle One አገልግሎት ውልና ተጨማሪ ደንቦች በGoogle One አጠቃቀምዎ ላይ ተፈጻሚ ናቸው። የእርስዎ የGoogle One አጠቃቀም ለዚህ የGoogle One አገልግሎት ውል እና የGoogle አገልግሎት ውል (ለዚህ የGoogle One አገልግሎት ውል ዓላማ ሲባል በአንድ ላይ «ደንቦች» ብለን የምንጠራቸው) ተገዢ እንደሆነ ይስማማሉ። ማስታወሻ፦ የGoogle ግላዊነት መመሪያው ውሂብ በዚህ አገልግሎት ውስጥ እንዴት እንደሚያዝ ይገልጻል።

በGoogle One አገልግሎት ውል እና በGoogle አገልግሎት ውል መካከል ማንኛውም ግጭት ቢኖር የGoogle One አገልግሎት ውል የበላይነት ይኖረዋል። በእንግሊዝኛው የደንቦቹ ስሪት እና ወደ ሌላ ቋንቋ በተተረጎመ ስሪት መካከል ማንኛውም ግጭት ካለ የእንግሊዝኛው ስሪት የበላይነት ይኖረዋል።

የእርስዎ የGoogle One መጠቀም በደንቦቹ እንዲስማሙ ይፈልግብዎታል፣ የGoogle One ዕቅድ አስተዳዳሪ ወይም Google One የሚጋራ የቤተሰብ ቡድን አባል ቢሆኑም። እባክዎ ደንቦቹን በጥንቃቄ ያንብቡ። አንዳንድ ምርቶች እና ባህሪያት በሁሉም አገሮች የሚገኙ ላይሆኑ ይችላሉ። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እባክዎ የGoogle One እገዛ ማዕከሉን ይመልከቱ።

2። አጠቃላይ የGoogle One መግለጫ

Google One የGoogle አገልግሎቶች እና ድጋፍ መድረሻ ለእርስዎ ለማቅረብ፣ ሽልማቶችንና ቅናሾችን ለማቅረብ እና አዲስ ባህሪያትንና ምርቶችን ለማግኘት በGoogle የቀረበ ነው።

የGoogle One ባህሪያት በGoogle Drive ውስጥ የሚገኙ የሚከፈልባቸው የማከማቻ ዕቅዶችን፣ እርስዎ ሊጠቀሙባቸው የሚችሏቸው የበርካታ Google ምርቶች የደንበኛ ድጋፍ፣ የቤተሰብ ማጋሪያ ባህሪያት፣ የሞባይል ምትኬ እና ወደነበረበት መመለስ እና ሌሎች በGoogle ወይም በሶስተኛ ወገኖች በኩል ለእርስዎ የቀረቡ ጥቅማጥቅሞችን ሊያካትቱ ይችላሉ። የእርስዎ የተጨማሪ የGoogle ምርቶች ወይም አገልግሎቶች አጠቃቀም እንዲህ ያሉ ምርቶችን ወይም አገልግሎቶችን ለሚመለከታቸው አገልግሎት ደንቦች ተገዢ ነው።

3. ክፍያ እና የደንበኝነ ምዝገባ

የGoogle One ዕቅድ አስተዳዳሪዎች ብቻ ናቸው አንድ የGoogle One አባልነትን መግዛት፣ ማላቅ፣ ስሪት ዝቅ ማድረግ ወይም መሰረዝ የሚችሉት። የእርስዎ የሚከፈልበት የGoogle One ደንበኝነት ምዝገባ በየGoogle Play አገልግሎት ውል፣ በተለይ «የደንበኝነት ምዝገባዎች» በሚለው ክፍል፣ መሠረት የተገዛ ነው። የGoogle One ደንበኝነት ምዝገባ ለመግዛት የGoogle Payments መለያ ያስፈልገዎታል፣ እና የGoogle Payments አገልግሎት ውል እና የGoogle Payments ግላዊነት ማስታወቂያን መቀበል አለበዎት።

የእርስዎ የGoogle One ደንበኝነት ምዝገባ እስኪሰረዝ ድረስ ይቀጥላል። የእርስዎ የGoogle One ደንበኝነት ምዝገባዎ ክፍያ በእነዚህ ደንቦች ውስጥ በግልጽ ከተፈቀደው በስተቀር ተመላሽ የማይደረግ መሆኑን ይስማማሉ።

ስራ ላይ የዋለው የGoogle One ዋጋ(ዎች) ልንቀይረው እንችላለን፣ ነገር ግን ቀደም ብለን ስለእነዚህ ለውጦች እናሳውቀዎታለን። እነዚህ ለውጦች የአሁኑ የክፍያ ጊዜዎ ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጣዩ ክፍያ ከማሳወቂያው በኋላ የሚከፈልበት ጊዜ ላይ ይተገበራሉ። እርስዎን ከማስከፈላችን በፊት ቢያንስ 30 ቀኖች አስቀድመን የዋጋ ጭማሬ ማሳወቂያ እንሰጠዎታለን፤ ከ30 ቀኖች ያነሰ ቅድሚያ ማስታወቂያ ከተሰጠዎት ለውጡ ከሚቀጥለው ክፍያ በኋላ ያለው ክፍያ ከመድረሱ በፊት አይተገበርም። በGoogle One ወይም በአዲሱ ዋጋ መቀጠል ካልፈለጉ በማንኛውም ጊዜ ከእርስዎ የGoogle Play ደንበኝነት ምዝገባዎች ቅንብሮች ሆነው ሊሰርዙ ወይም ስሪት ዝቅ ሊያደርጉ ይችላሉ። የእርስዎ ስረዛ ወይም ስሪትን ዝቅ ማድረግ ከአሁኑ የአገልግሎት ጊዜ በኋላ ባለው ቀጣዩ የማስከፈያ ጊዜ ላይ ይተገበራል።

የአውታረ መረብ አገልግሎት አቅራቢዎ ወይም ሌላ ሶስተኛ ወገን ባቀረበው ስፖንሰር የተደረግ ዕቅድ (ምንም ሆነ ምን «ስፖንሰር የተደረገ ዕቅድ») በኩል Google One ሊያገኙ ይችላሉ። ለማናቸውም ስፖንሰር የተደረጉ ዕቅዶች ያለ ክፍያ የሚወሰነው በስፖንሰር አድራጊው ሲሆን የዋጋ አሰጣጥ መረጃንና ሌሎች ዝርዝሮችን በተመለከተ የእነሱን ደንቦች መመልከት አለብዎት። ስፖንሰር የተደረገው ዕቅድዎን በስፖንሰር አድራጊዎ በኩል ማግኘት ይችላሉ፣ ወይም በቀጥታ ከGoogle One ሆነው የአልቅ አማራጩን በመምረጥ ማግኘት ይችላሉ፣ በGoogle One ሲሆን የክፍያ እና ደንበኝነት ምዝገባ ደንቦቹ በማላቅዎ ላይ ተግባራዊ ይደረጋሉ።

4. የደንበኛ ድጋፍ

Google One በተለያዩ የGoogle ምርቶች እና አገልግሎቶች ላይ የደንበኛ ድጋፍ («የደንበኛ ድጋፍ») ያቀርብልዎታል። የደንበኛ ድጋፍን ከደረሱ ተወካዩ/ዮቹ እና ስርዓቶቹ የGoogle አገልግሎቶች አጠቃቀምዎን በተመለከተ በGoogle ግላዊነት መመሪያው መሠረት እና የደንበኛ ድጋፍን ለእርስዎ ለማቅረብ እና የተጠየቁትን ችግሮች ለመፍታት ዓላማዎች አስፈላጊውን መረጃ እንደሚደርሱ እውቅና ይሰጣሉ።

የደንበኛ ድጋፍ እርስዎን በድጋፍ ጥያቄዎ ላይ መርዳት ያልቻለ እንደሆነ ጥያቄ ወደተነሳበት የGoogle ምርት ደንበኛ ድጋፍ አገልግሎት ልናስተላልፍዎ ወይም ልንመራዎ እንችላለን። ይህ Google One ለተጠየቀው የGoogle ምርት ወይም አገልግሎት የደንበኛ ድጋፍ የማይሰጥባቸው አብነቶችን ያካትታል።

የእርስዎ የGoogle One ደንበኝነት ምዝገባ ከተሰረዘ ወይም ከታገደ ያልተፈታው የደንበኛ ድጋፍ ችግሮችዎ እንዲሁም ሊታገዱ ይችላሉ፣ እና አንዴ የደንበኝነት ምዝገባዎ ወደነበረበት ከተመለሰ በኋላ አዲስ ጥያቄ ማንሳት ሊኖርብዎት ይችላል።

5. የአባል ጥቅማጥቅሞች

Google One ነጻ ወይም ቅናሽ የተደረገባቸው ይዘት፣ ምርቶች እና አገልግሎቶች («የአባል ጥቅማጥቅሞች») ሊሰጠዎት ይችላሉ። የአባል ጥቅማጥቅሞች በአገር፣ አቅርቦት ወይም ሌሎች ሁኔታዎች መሠረት የተገደቡ ሊሆኑ ይችላሉ፣ እና ሁሉም የአባል ጥቅማጥቅሞች አይደሉም ለሁሉም የGoogle One ደንበኝነት ምዝገባዎች የሚገኙ የሚሆኑት። በተጨማሪም፣ በቤተሰብ ማጋራት ሲሆን (ከታች «ቤተሰብ» በሚለው ክፍል ውስጥ በተገለጸው መሠረት) አንዳንድ የአባል ጥቅማጥቅሞች ለGoogle One ዕቅድ አስተዳዳሪ የተገደቡ ሊሆኑ ይችላሉ፣ እና አንዳንድ የአባል ጥቅማጥቅሞች በቤተሰብዎ አባላት ወይም መጀመሪያ ለወሰደው የቤተሰብ አባልዎ ብቻ ሊወሰዱ የሚችሉ ሊሆኑ ይችላሉ። አንዳንድ የአባል ጥቅማጥቅሞች የልጆች እና ታዳጊዎች በሆኑ የGoogle መለያዎች ሊወሰዱ አይችሉም።

የሶስተኛ ወገኖች አገልግሎቶች ወይም ይዘት በGoogle One በኩል ለእርስዎ እንደ የአባል ጥቅማጥቅሞች ለማቅረብ ከእነሱ ጋር ልንሰራ እንችላለን። በሶስተኛ ወገን የቀረበው የአባል ጥቅማጥቅሙ ለመውሰድ Google በGoogle ግላዊነት መመሪያ መሠረት የመውሰድ ጥያቄዎችን ለማስሄድ የሚያስፈልገውን ማንኛውም የግል መረጃ ለሶስተኛ ወገኑ ሊሰጥ እንደሚችል እውቅና ይሰጣሉ። እርስዎ የማንኛውም ሶስተኛ ወገን የአባል ጥቅማጥቅሞችን መጠቀም እንዲህ ባለው የሶስተኛ ወገን አጠቃቀም ደንቦች፣ የፈቃድ ስምምነት፣ የግላዊነት መመሪያ ወይም ሌላ እንዲህ ያለ ስምምነት ተገዢ ሊሆን ይችላል።

Google ማንኛውም የሶስተኛ ወገን የአባል ጥቅማጥቅሞችን በተመለከተ ጥራት፣ ትክክለኝነት፣ ውጤታማነት፣ ደህንነት፣ የሶስተኛ ወገን መብቶች አለመጣስና ማናቸውም የሚመለከታቸውን ህጎችና ደንቦች ማክበር ጨምሮ ማንኛውም አይነት ጉዳይ ላይ የዋስትና፣ የሁኔታ ወይም የውክልና ኃላፊነት አይቀበልም። እነዚህ ደንቦች እንዲህ ካሉ ሶስተኛ ወገን አቅራቢዎች ጋር ባለዎት ህጋዊ ግንኙነት ላይ ተጽዕኖ አይፈጥሩም።

6. ቤተሰቦች

የDrive ማከማቻ ቦታ ጨምሮ የተወሰኑ የGoogle One ባህሪያት ካለዎት ለቤተሰብ ቡድንዎ ሊጋሩ ይችላሉ («ቤተሰብ ማጋርት»)። የቤተሰብ ቡድንዎ እንዲሁም ለእርስዎ የሚገኙ የተደረጉ የአባል ጥቅማጥቅሞችን ሊቀበልና ሊወስድ ይችላል። እንዲህ ያሉ ባህሪያትን ለቤተሰብ ቡድንዎ ማጋራት ካልፈለጉ ቤተሰብ ማጋራት ለGoogle One ማሰናከል ወይም ከቤተሰብ ቡድንዎ መውጣት አለብዎት። የGoogle One ዕቅድ አስተዳዳሪዎች ብቻ ናቸው የቤተሰብ አባላትን ወደ Google One ማከል፣ እና በGoogle One አባልነት ላይ የቤተሰብ ማጋራትን ማንቃት ወይም ማሰናከል የሚችሉት።

እርስዎ በGoogle One ላይ የአንድ ቤተሰብ ቡድን አካል ከሆኑ የቤተሰብ ቡድንዎ አባላት ስለእርስዎ የተወሰነ መረጃ ማየት ይችላሉ። የቤተሰብ ማጋራት በነቃለት Google One አንድ የቤተሰብ ቡድን ከተቀላቀሉ ሌሎች የቤተሰቡ ቡድኑ አባላት እና ተጋባዦች የእርስዎን ስም፣ ፎቶ፣ የኢሜይል አድራሻ እና በGoogle Drive ውስጥ የሚጠቀሙበት የቦታ መጠን ሊያዩ ይችላሉ። የቤተሰብ ቡድን አባላት እንዲሁም የቡድን ጥቅማጥቅም በአንድ የቤተሰብ አባል ተወስዶ ከሆነ ማየት ይችላሉ።

እርስዎ በቤተሰብ ቡድንዎ ውስጥ የGoogle One ዕቅድ አስተዳዳሪ ከሆኑ እና የቤተሰብ ማጋራትን ካሰናከሉ ወይም ከቤተሰብ ቡድንዎ ከወጡ ሌሎች የቤተሰብ ቡድንዎ አባላት የGoogle One መዳረሻን ያጣሉ። በGoogle One ዕቅድ አስተዳዳሪዎ አማካኝነት በቤተሰብ ማጋራት በኩል የGoogle One መዳረሻ የተሰጠዎት ከሆኑ የቤተሰብ ቡድንዎን ትተው ከወጡ ወይም የGoogle One ዕቅድ አስተዳዳሪዎ የቤተሰብ ማጋራቱን ካሰናከሉ ወይም ከቤተሰብ ቡድኑ ከወጡ እርስዎ የGoogle One መዳረሻ ያጣሉ።

7. የሞባይል ምትኬ እና ወደነበረበት መመለስ

Google One ሞባይል መሣሪያዎችን እና ሞባይል ዕቅዶችን ለማጣራት የተሻሻለ የውሂብ ምትኬ እና ወደነበረበት መመለስ («ምትኬ እና ወደነበረበት መመለስ») ተግባር ሊያቀርብልዎ ይችላል። ምትኬ እና ወደነበረበት መመለስን መጠቀም እንደ የGoogle ፎቶዎች እና የAndroid መልዕክቶች ያሉ ተጨማሪ መተግበሪያዎችን መጫን እና ገቢር ማድረግ ሊያስፈልግ ይችላል። በማንኛውም ጊዜ በGoogle One መተግበሪያው ውስጥ ወይም በone.google.com ላይ የምትኬ እና ወደነበረበት የመመለስ አማራጮችዎን መቀየር ይችላሉ። የእርስዎ የGoogle One አባልነት ከታገደ ወይም ከተሰረዘ በAndroid ምትኬ መመሪያዎች መሠረት ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ወደ ምትኬ እና ወደነበረበት መመለስ የተቀመጠ ውሂብ መዳረሻ ሊያጡ ይችላሉ።

8. ስፖንሰር የተደረጉ ዕቅዶች

እንደ የሞባይል አገልግሎት አቅራቢ ወይም የበይነመረብ አገልግሎት አቅራቢ ባለ Google ያልሆነ ስፖንሰር አድራጊ ወገን በቀረበ ስፖንሰር የተደረገ ዕቅድ በኩል የGoogle One መዳረሻ ሊቀርብልዎ ይችላል። ለእርስዎ በሚገኙ የGoogle One ባህሪያት እና የስፖንሰር የተደረገ ዕቅድዎ ደንቦች ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እባክዎ የስፖንሰር አድራጊ ወገኑ አገልግሎት ውል ይመልከቱ። ለእርስዎ የሚገኙት የGoogle One ባህሪያት በስፖንሰር የተደረገ ዕቅድዎ መሠረት ሊለያዩ እንደሚችሉ ልብ ይበሉ። በስፖንሰር የተደረገ ዕቅድ በኩል ያለው የእርስዎ የGoogle One ብቁነት እና መዳረሻ በስፖንሰር አድራጊ ወገኑ የሚወሰን ሲሆን ስፖንሰር የተደረገ ዕቅድዎ በማንኛውም ጊዜ በስፖንሰር አድራጊው ሊታገድ ወይም ሊቋረጥ ይችላል።

9. ግላዊነት

Google በዚህ ውል እና በGoogle ግላዊነት መመሪያው መሠረት Google Oneን ለእርስዎ ለማቅረብ በእርስዎ የሚቀርብ መረጃን ሊሰበስብና ሊጠቀምበት ይችላል። Google Oneን ለመጠገን እና ለማሻሻል ስለGoogle One አጠቃቀምዎ መረጃ ልንሰበስብና ልንጠቀም እንችላለን። እንዲሁም Google Oneን ለማሻሻል ወይም ጥቅማጥቅሞችን ለእርስዎ ለማቅረብ የሌሎች Google አገልግሎቶች አጠቃቀምዎ መረጃን ልንጠቀምም እንችላለን፤ myaccount.google.com ላይ የGoogle እንቅስቃሴዎ አሰባሰብ እና አጠቃቀም መቆጣጠር ይችላሉ።

የሶስተኛ ወገን የአባል ጥቅማጥቅሞች ብቁነትዎን ለመወሰን ወይም ለማሰጠት ወይም ደግሞ የአንድ ስፖንሰር የተደረገ ዕቅድ ብቁነትዎ ብቁነት ለመወሰን ጨምሮ Google Oneን ለማቅረብ የሚያስፈልገው ስለእርስዎ የተወሰነ መረጃ ለሶስተኛ ወገኖች ልናጋራ እንችላለን። እንዲሁም የቤተሰብ ቡድንዎ የGoogle One ሁኔታ እና ደንበኝነት ምዝገባ መረጃ ለማቅረብ ስለእርስዎ ያለ መረጃ ለቤተሰብ ቡድንዎ ልናጋራ እንችላለን።

ከGoogle One አጠቃቀምዎ ጋር በተያያዘ የአገልግሎት ማስታወቂያዎች፣ አስተዳደራዊ መልዕክቶች እና ሌላ መረጃ ልንልክልዎ እንችላለን። እንዲሁም ከአባል ጥቅማጥቅሞችዎ ጋር የተጎዳኙ ኢሜይሎችን እና የመሣሪያ ማሳወቂያዎችን ልንልክልዎ እንችላለን። ከአንዳንድ እነዚህ ተግባቦቶች መርጠው መውጣት ይችላሉ።

10. ለውጦች

በGoogle One ላይ ለውጦችን የማድረግ መብታችን የተጠበቀ ነው፣ እና Google One ተጨማሪ ወይም የተለዩ ባህሪያት ለማቅረብ ሊከለስ ይችላል። የGoogle One ደንበኝነት ምዝገባዎ ለደንበኝነት በተመዘገቡበት ጊዜ ላይ ለነበረው የGoogle One ቅርጽ መሆኑን ይስማማሉ። እንዲሁም ከጊዜ ወደ ጊዜ ለGoogle One የተለያዩ ውልን እና እርከኖችን ልናቀርብ እንችላለን፣ እና እንዲህ ላሉ የደንቦች ወይም እርከኖች ደንበኝነት ምዝገባ ክፍያ ሊለይ ይችላል።

በGoogle One ወይም በዚህ ውል ላይ ምክንያታዊ በሆነ ደረጃ በGoogle One አጠቃቀምዎ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያመጣሉ ብለን የምናምናቸው ጉልህ ለውጦች ካሉ እናሳውቀዎታለን። ይሁንና፣ ማሳወቂያ ሳንሰጥ በGoogle One ላይ ለውጦችን ማድረግ የሚኖርብን ጊዜዎች አሉ። እነዚህ የGoogle One ደህንነትንና የመስራት ብቃቱን ማረጋገጥ፣ አላግባብ መጠቀምን መከላከል ወይም ህጋዊ ግዴታዎችን ማሟላት ለሚኖሩብን ጊዜያት የተገደቡ ናቸው።

11. ስረዛ እና ማቋረጥ

እርስዎ የGoogle One ዕቅድ አስተዳዳሪ ከሆኑ በማንኛውም ጊዜ የGoogle Play ደንበኝነት ምዝገባ ቅንብሮችዎን በመጎብኘት የGoogle One አባልነትዎን መሰረዝ ይችላሉ። የደንበኝነት ምዝገባዎን ከሰረዙ ለተቀረው የነባሩ ደንበኝነት ምዝገባዎ ጊዜ የGoogle One መዳረሻዎ እንደኖረዎት ይቀጥላሉ።

በተጨማሪም በየአገልግሎት ስረዛ በኩል Google Oneን ለመሰረዝ ከመረጡ ለተቀረው የደንበኝነት ምዝገባዎ ጊዜ ምንም ገንዘብ ተመላሽ ሳይደረግልዎ ወዲያውኑ የGoogle One አገልግሎቶች እና ተግባራት መዳረሻ ሊያጡ እንደሚችሉ ይስማማሉ። ለተቀረው የደንበኝነት ምዝገባዎ ጊዜ የGoogle One አገልግሎቶችን ማቆየት ከመረጡ እባክዎ በምትኩ የደንበኝነት ምዝገባዎን ይሰርዙ።

Google በማንኛውም ጊዜ ለዚህ ውል ጥሰት ጨምሮ Google Oneን ለእርስዎ ማቅረብ ሊያቆም ይችላል። ስፖንሰር የተደረገ ዕቅድ ላይ ከሆኑ የGoogle One መዳረሻዎ እንዲሁም በስፖንሰር አድራጊ ወገንዎ ሊታገድ ወይም ሊቋረጥ ይችላል።

Google ለእርስዎ ምክንያታዊ ማስታወቂያ ሰጥቶ በማንኛውም ጊዜ Google Oneን የማገድ ወይም የማቋረጥ መብቱ የተጠበቀ ነው።